የ አዲስ ነገር ልዩ ጥንቅር...
በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆይቶ እነሆ በሪፐብሊካኖች አሸናፊነት በ 51 ለ 49 ድምፅ የአሜሪካ ኮንግረስ ህጉን አፅድቆታል፡፡
ማሻሻያው ህግ ሆኖ ለመውጣት አንድ እርከን ቢቀረውም የሚቀየር ነገር ግን እምብዛም ሊኖር አይችልም እየተባለ ነው፤
ትራምፕ በትዊተር ድረ ገፃቸው “በታክስ አከፋፈሉ ላይ ጥቂት ለውጥ በማምጣት እና ትንሽ አሀዝን በመቀየር መካከለኛ እና ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያገኙ እናደርጋለን፤ ባለሃብቶችም ብዙ ሰራተኞችን ይቀጥራሉ ብለዋል፡፡
ትራምፕ እንዲህ ቢሉም ገለልተኛ ነው የሚባለው የኮንግረስ በጀት ጽህፈት ቤት የሚባለው ተቋም ባወጣው ሪፖርት እቅዱ ደሀውን የበለጠ ሲያደኸይ ለባለፀጋው ደግሞ ሀብት ይጨምርለታል ብሏል፡፡
ሪፖርቱ እንደሚለው አመታዊ ገቢያቸው ከ30ሺህ ዶላር በታች የሆኑ አሜሪካውያን የበለጠ ሲጎዱ በዓመት ከ100 ሺህ ዶላር በላይ የሚያገኙ ደግሞ የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
በዚህ ረቂቅ እቅድ የዜጎችን ማንነት እየለየ ይተገበር የነበረውን የታክስ ቅነሳ አካሄድ ውድቅ ያደረገ ሲሆን ብዙ የክሬዲት አይነቶችንም አስወግዷል፡፡
እንደውም የታክስ ቅነሳ የሚደረገው በበጎ ምግባር ለተሰማሩ ወገኖች ሲሆን ይህም ቢሆን ሐብታሙን የሚጠቅም ነው እየተባለ ነው፡፡ ሌላው ለሐብታሞች የተፈቀደው ነገር ደግሞ የ20 በመቶ የታክስ ቅናሽ ነው ተብሏል፡፡
Visit our facebook page: www.facebook.com/ebsnewsroom