- በመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ማስፈራሪያ ዛቻ የደረሳት ኢራን አልበገርም በማለት 2000 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘግ ሚሳኤል አስወነጨፈች ፣ድርጊቱ ያች ሀገር ከእስራኤል ጋር ያላትን ፍጥጫ እንዳያጦዘው ተሰግቷል፡፡
- ለአራተኛ የስልጣን ዘመን በምርጫ የተሳተፉት የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጄላ ሜርኬል ድል ቀንቷቸዋል ፡፡ ለድላቸውም መራጮች በስደተኞች ጉዳይ ያላቸውን አቋም መቀየራቸው እንደምክንያት እየተጠቀሰ ነው፡፡
- የሳዑዲ አረብያ መንግሥት ለሴቶች የተሻለ መብት መስጠት በአገሪቱ ብሔራዊ በዓል ላይ ከወንዶች እኩል አደባባይ ወጥተው እንዲያከብሩ ፈቀደች፡፡ እርምጃው የሳዑዲ አረቢያን ጉሳዊ መንግሥት ያዝኩት ያለው እርምጃ አካል ቢሆንም የሳዑዲ ሴቶች ተጨማሪ መብቶቻቸውን እየጠየቁ ነው፡፡
- የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስአይድ) በአፍሪካ ሀገራት ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የወባ በሽታ ለመግታትና ብሎም ለማጥፋት ተጨማሪ ሀገራትን በፕሮግራሜ ውስጥ አስገብቻለሁ ሲል በሃላፊው ማርክ ግሪን በኩል አሳውቋል፡፡በበጀት መልክ መድቦ ሊንቀሳቀስባቸው ያሰባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ካሜሮንን፣ ኮትዲቫርን ፣ኒጀርን እና ሴራሊዮንን መሆኑ ተነግሯል
- ታላቋ ብሪታንያ የአሲድ ጥቃት ላደረሰ ግለሰብ ከፍተኛ የእስር ቅጣት እንደምትጥል ካሳወቀች 2ወር እንኳ ባይሞላትም ድርጊቱ ሊቆም እንዳልቻለ የአገሪቱ ፖሊስ አሳውቋል፡፡ በአንድ የገበያ አዳራሹ መውጫና መግቢያ ላይ በትርምስምስ መሃል ዝርፊያን ሊፈጽሙ የፈለጉ ወጣቶች በሰዎች ፊት ላይ አቃጣይ ፈሳሽ ረጭተው ስድስት ሰዎችን እንደጎዱ ታውቋል፡፡ ፖሊስ ክትትል አድርጎ አንድ ወንጀለኛ ብቻ ቢይዝም ቀሪዎቹ አምስቱ ገና እንዳልተያዙ አሳውቋል፡፡
Monday, September 25, 2017
የአዲስ ነገር የአለም አበይት ክስተቶች!
የ አዲስ ነገር ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...