ካሳሁን
መብራቱ - ለአዲስነገር ከዋሽንግተን ዲሲ

በቅርቡ እንኳን አሜሪካ በግሏ እና ከተባበሩት መንግስታት ጋር አብራ የሰሜን ኮሪያን ኢኮኖሚ
የሚሸነቁጥ ማዕቀብ ቢያወርዱባትም ለሌላኛው የሚሳኤል ሙከራ እየተዘጋጀች መሆኗን ፍንጭ ሰጥታለች፡፡
የነዳጅ እና የጨርቃ ጨርቅ
ምርቶቿ ከሀገሯ ወጥተው በዓለም ገበያ እንዳይሸጡ ሲታገዱባት መውጫ ቀዳዳ አለኝ ብላ ያሳወቀችው አለማቀፍ የውጭ ባንኮችን በሰለጠኑ
ባለሙያዎቿ ማዘረፍና ለፕሮግራሟ ድጎማ ማድረግ ነበር፡፡
ታዲያ ፕሬዝዳንት ትራምፕ
ከአሁን አሁን ለሃሳቤ ተገዛች ለቁጣዬ ደነገጠች እያሉ ቢጠባበቁም ያሰቡት ሳይሳካ እዚህ ደርሰዋል፡፡ በንዴት ቃለ አጠፋታለሁ እያሉ
ሲዝቱም ተሰምቷል፡፡
አሁን ግን ከአማካሪዎቼ
ጋር ተወያይቼ ያመጣሁት የቅጣት ሃሳብ ብርቱ ነው በማለት አዲስ ሰሜን ኮሪያን የሚመለከት ሰነድ ፈርመው ስራ ላይ እንዲውል አዘዋል፡፡
ፊርማቸው ያረፈበት አዲስ
ተፈጻሚ ህግ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የሚሰሩ ሀገራት ብቻ ሳይሆን ተቋማት ግንኙነታቸውን ማቆም እንዳለባቸው የሚደነግግ ነው፡፡
በየትኛውም ሀገር የሚገኙ
የቢዝነስ ተቋማት በቀጥታም ይሁን በስውር ከሰሜን ኮሪያ ጋር የሚያነካካ ስራ ካላቸው ይህንኑ ማቆም እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡
እነሱም ጥቅማችን ይቀራል
ብለው ካሰቡ ከአሜሪካ ጋር የሚኖራቸውም ቁርኝት ይቋረጥባቸዋል ብለዋል ትራምፕ፡፡ በስተመጨረሻም ቢሆን ትራምፕና አስተዳደራቸው ያፈለቁት
አዲሱ የመቅጫ ሰነድ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
በተለይ የቻይና እናየሌሎች
የኢሲያ ሀገራት ብሄራዊ ባንኮች ከሰሜን ኮሪያ እየፈረሰች እና እየደኸየች
ያለች ሀገር በመሆኗ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር መነገድ ኪሳራና ከአሜሪካ ጋር መቃቃር ደግሞ ስራን በገዛ እጅ ማጣት ነው ያሉ ድርጅቶች ወዲያው ይሁንታቸውን
ለትራምፕ አሳይተዋል በማለት ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡