Monday, October 9, 2017

የውቅያኖስ ቆሻሻ ፅዳት

የአለምችን ውቅያኖሶች እጅግ በፕላስቲክ ቆሻሻዎች እየተሸፈኑ ነው ሲል ስጋቱን የገለፀው የአውሮፓ ኮሚሽን የድርሻዮን አበርክቼ ላፅዳ በማለት የ650 ሚሊዮን ዶለር በጀት አፅድቋል፡፡ ከየመኖሪያ አካባቢና ከመዝናኛ ስፍራዎች አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ ውለው መሬት ላይ የሚጣሉት የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ውቅያኖስ በውሃ ተወስደው እዛ ይገኛሉ ሲል ኮሚሽኑ በሳተላይት ያነሳውን ምስል አሳይቷል፡፡ እነዚህ የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በየአመቱ ካልተሰበሰቡና ከውሃው ካልራቁ ከ30 አመታት በኋላ ህንድና አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጣቸው ከሚይዙት አሳና ሌሎች ነፍሳት በበለጠ ፕላስቲክ ቆሻሻዎቹ ልቀው ይታይሉ የሚልም ስጋት አለው፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...