ካሳሁን መብራቱ - ለአዲስነገር ከዋሽንግተን ዲሲ
በእንስት ስም የምትጠራው የማሪያ ወጀብ የፓርቶሪኮንና የዶሚኒካን ሀገራትን ቶሎ እንዳያገግሙ አድርጋ አፈራርሳቸዋለች ተብላለች፡፡ ዝናብን ከፈጣን አውሎ ንፋስ ጋር ቀላቅላ ምድሪቱን ያጥለቀለቀችው የማሪያ ወጀብ ትላልቅ ህንፃዎች በመጉዳት አስፋልቶች አፈራርሳለች በተለይ Porto rico በተባለች የዴሴት ሀገር ላይ የከፋ ጉዳት አድርሳ ህይወት ነጥቃለች፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ተቋቁሞ ለህዝቦቹ የኤሌክትሪከ አገልግሎት የሚሰጠው ብቸኛው የመብራት ማከፋፈያ ማእከሏ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለማደስና ዳግም ብርሃን ለመርጨት ቢያንስ ከ4-6 ወራት ይፈጃል ተብሏል፡፡