ካሜሮን በእንግሊዘኛ የሚተላለፍ የቴሌቪዥን ጣቢያን ዘግቻለሁ ስትል አስታወቃለች፡፡ ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም በሁለት የአውሮፓ ሀገራትም በፈረንሳይና በእንግሊዘኛ ተገዝታ የነበረ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት ቋንቋቸውን አላምደው ተመልሰዋል እናም ደቡባዊ ካሜሮንአውያን የእንግሊዝ ተገዢ ስለነበሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ይግደለን የሚሉና ቅድሚያ የሚሰጡ ናቸው፡፡
ታዲያ ሁለቱ የአንድ ሀገር ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች በጋራ እንኑር ተባብለው እ.አ.አ. 1916 ከተዋሃዱ ወዲህ የፈረንሳይ ተገዢዎቹ በርከት በማለታቸው ተጽዕኖ ሲያሳድሩባቸው ኖረዋል ተብሏል፡፡
በሀገሪቱ የሚተላለፉ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ድራማዎችና የመንግስት መግለጫዎች በፈረንሳይኛ ቋንቋ እንዲሆንም ተጠቁሟል፡፡
ታዲያ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ህዝቦች ወኪል የሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያስተላልፉበትና ድምጻቸውን የሚተነፍሱበት አንድያ ቴሌቪዥናቸውን ተነጥቀዋል ሲሉ የሀገሪቱ ጋዜጦች እየፃፉ ነው፡፡ ምክንያቱ ደሞ የሀገሪቱን መንግስት በእንግሊዘኛ ፕሮግራማቸው ወቅሰዋል ፤ ችግራቸውንም የዓለም ህዝብም እንደያውቀው አድርገዋል ተብለው ነው፡፡