Thursday, August 31, 2017

ቻይና እስካሁን የታሪክ ትምህርት የሚሰጥባቸው መጽሃፎቼ ላይ ስህተት አግኝቻለሁ ብላ እርማት ላይ ናት፡፡


ቻይና እስካሁን ታሪክ ትምህርት የሚሰጥባቸው መጽሃፎቼ ላይ ስህተት አግኝቻለሁ ብላ እርማት ላይ ናት፡፡ ቻይና እንደሌሎች የዓለም ሀገራት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ የተሳተፈች ሲሆን የቀድሞ የታሪክ መጽሃፍ ላይ ከጃፓን ጋር ተዋጋች  ተብሎ የተፃፈው ለ8 ዓመታት ብቻ ነበር ነገር ግን የጃፓን ወታደሮች ወረራ አድርገው  የሰሜን  ምስራቅ  ቻይና መሬት አካል የሆነችውን ማንቹሪያን የወሰዱበት እ.አ.አ. 1931 በመሆኑ ጦርነቱ  የወሰደው ጊዜ 14 ዓመታትን ነው ተብሎ በመጪው አዲስ መጽሃፍ ይካተታል ተብሏል፡፡
ብዙዎቹ ግን አባቶቻችን የሰነዱትን ታሪክ የማኦ ፖሊቲካ ፓርቲ የስልጣኑን ዘመኑን ለማራዘም ሲል ሊከልሰው ነው በማለት ላይ ናቸው፡፡ ቻይናን እያስተዳደረ ያለው መንግሥት ከ 50 ዓመታት በላይ የዘለቀና እድሜ ጠገብ በመሆኑ የቻይና  ብልጽግናንና ዝናን እኔ ነኝ ያመጣሁት ወደ ማለቱ እራሱን እየቃየረ እንደሆነም ተወቅሷል፡፡
በቀጣዩ አመታት የቻይና የህዝብ መዝሙር ከመንግስታዊ ስርዓት ባሻገር በየቀብር ስነስርአትና በሌሎች ማህበራዊ ክንወኖች ላይ  እንዲዘመር የማድረግ አላማ እንዳለውም ታውቋል፡፡




የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...