እነዚህ መንገዶች የውጭ ሀገር ዜጎችን ማመላለሻ መስመሮች ናቸውና እባካችሁ ስማችን ዳግም ጥላሸት እንዲቀባ አታድርጉት ብለው ተማጽነዋል፡፡
የዙምባቡዌ ፖሊሶች ለእርዳታ ሄደው ገንዘብ ተቀብለው የሚመጡ ናቸው ተብሎ ለብዙ አመታት የሙሰኝነታቸው ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ትችቶች ደርሰውባቸው ያውቃሉ፡፡አሁን ደግሞ ብሶበት መታየቱን ሙጋቤ በአንደበታቸው መስክረዋል ሲል ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል፡፡
ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈጸም ከተፈለገ ለህዝቡ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወገኖች ማህበር ፈጥረው በጋራ በመንቀሳቀስ ሙሰኞችን ማጋለጡ ተገቢ ይሆናል በማለት ሙጋቤ ሰሚ ካለ ብለው መክረዋል፡፡