
ወጣቶቼና ነፍሰጦር ዜጎቼ ከምግብ ይልቅ ሲጋራና መጠጥ ይመቻቸዋል ያለችው ዛምቢያ የተጋነነ የታክስ ጭማሪ ልታደርግ መሆኗን አሳውቃለች፡፡ በጦና ታሞ አልጋ የያዘ ወጣቷ ለአግሙ መግባት ከመድሃኒትና ከምግብ ይበልጥ እንዲቀርብላት የሚፈልገው ሱስ አስያዥ የሆነውን ሲጋራ ሲሆን ይህ ደግሞ ጤናማነት አይደለም ሱሉ የሀገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ለህግ አውጪዎች መረጃ ሰጥተዋል በተለይ በዚህች ሀገር የሞኖሩ ብዙሃን ወጣቶች ስራ አጥ በመሆናቸው መንግስት እንዳያማርሩብኝ ብሎ ለአመታት የዋጋ ቅናሽ በተለያዩ ሸቀጦች ላይ እንዲደረግ ህግ ደንግጎ ነበር፡፡
እናም ሲጋራና መጠጦችን የሚሸጡ ነጋዴዎች ባያዋጣቸውም ህጉን ለማክበር ሲሉ ለገበያ እንደሚያቀርቡም ይነገራል፡፡በመጨረሻም ጊዜ ነቅቻለሁ ያለው የዛምቢያ መንግስት ልዩ ቅናሹ ለትምህርት ቤቶች እንጂ ለነዚህ ገዳይ ምርቶች አልነበረም በማለት መሳሳቱን አምኗል፡፡ ከመጪው ወራት ጀምሮ የ70 በመቶ የታክስ ጭማሪ በሲጋራና በፈሳሽ አልኮሎች ላይ ተደማሪ ይሆናል፡፡