Friday, September 1, 2017

ለአመታት ከሰርን እንጂ ትርፋማ ሆነናል የሚል ዜና አሰምተው የማያውቁት የደቡብ አፍሪካ አየር መንገዶች

ለተከታታይ አመታት ከሰርን እንጂ ትርፋማ ሆነናል የሚል መልካም ዜና አሰምተው የማያውቁት 3ቱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት አየር መንገዶች ወደ አንድ ሚዋሀዱ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
የሀገር ውስጥ በረራ የሚያካሂዱበትና የዓለማቀፍ አየር መንገዶች በአንድ  ስም  ተጠርተውና  በአንድ ጠንካራ መሪ እየተዳደሩ ትርፋማ እንዲሆኑ ተወጥኗል፡፡ አየር መንገዶቹን ከማዋሃድ  በተጨማሪም 25 በመቶ የሚሆነውን የድርጅቱ  ድርሻ ለግል ባለሀብቶች  በመሸጥ የገንዘብ መጠኑን ለማሳደግ ውጥን ላይ ናቸው፡፡

SOUTH AFRICAN AIRWAYS ARM MANGO እና SAA EXPRESS   ሀገር በቀል አየር መንገዶች ናቸው ፡፡ ተጨፍልቀው አንድ ጠንካራ የትራንስፖርት ተቋም ለመመስረት የተዘጋጁት እነዚህ አየር መንገዶች የሀገር ውስጡን በረራና የዓለማቀፍን በጋራ በማመላለስ ትርፍ እንጂ ክስረት የሚለው ቃል ከድርጅቱ እንዲወጣ ይጥራሉ  ያሉት PUBLIC ENTERPRICE MINISTER የሀገሪቱ ላይን ብራውን ናቸው፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...