የ193 ሀገራትን ውክልና ወስዶ ጉዳያቸውን የሚያስፈፅመው የመንግስታቱ ድርጅት በ ኒውዮርክ ጠቅላላ ጉባኤ ተቀምጧል:: ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝደንት ትራምፕ በአባል ሀገራቱ ወኪሎች ፊት ባደረጉት ንግ ግ ር ዩኤን የሚጠበቅበትን ያህል እየሰራና ወደ ፊት እየተራመደ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ መንግስታት ድርጅት ይጠበቃል የሚሉትን ጉዮች በዝርዝር ተናግረዋል፤
ለመጀመሪያ ጊዜ ማለት ይቻላል በተፃፈና ባነበቡት ንግ ግራቸው ድርጅቱ በየአመቱ የሚሰበሰበውን የአባልነት መዋጮ ከሰሜን አሜርካ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ሀገራት እኩል መጠን ያለው መሆን አለበት ሲሉም ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ባሻገርም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም ለማስከበር የሚልካቸው ወታደሮች ቁጥራቸው ሳይበዛ አሊያም ሳያንስ አስፈላጊው ጥናት ተደርጎ በመመደብ የገንዘብ እጥረቱን ይቀርፋል በማለትም መክረው ከፖለቲካው ወጣ ብለው የንግድ ሰው መሆናቸውንም ጠቆም አድርገዋል፡፡ ዩኤን የቆየ አሰራሩን መቀየር ካልቻለና በየአመቱ ተመሳሳይ መንገድ የሚከተል ከሆነ እጃችንን ሰብስብ አድርገን ገንዘባችንን ለህዝባችን ለማዋል እንገደዳለን በማለትም ዋና ፀሀፊውን አንቶኒዮ ጉቴርዝን ወረፍ አድርገዋል፡፡

ትራምፕ በናቶ አጠቃላይ አመታዊ የውይይት መድረክ ላይ በተገኙም ጊዜም ተመሳሳይ ይዘት ያለው የማስፈራሪያና የማስጠንቀቂያ ፅሁፍ ማንበባቸው ይታወሳል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ላይ እየተከሰተ ባለው የአለማችን አለመረጋጋት ሳቢያ ለሀገራት እርዳታ በመስጠት ላይ ተጠምዷል፡፡ እናም እ.አ.አ ከ2000 ጀምሮ ከአጠቃላይ አመታዊ በጀቱ የ140 በመቶ ጭማሪ ማደጉም ተገልፃል፡፡
በየቦታው ለሚከፈተው ቢሮውም የሰራተኛ ጭማሪ በማድረጉ አባል ሀገራቱ የመዋጮው ገንዘብ ላይ ቅር መሰኘታቸውን በፅሁፍ ማስገባታቸውን ዋና ፀሃፊው ጉትሬዝ በዚህ መድረክ ላይ መስክረዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለ በቂ ምክንያት የሚወጣ ገንዘብን የሚባክን ጉልበት እንዳይኖር አዲስ
አሰራር እንዘርጋ ተባብለውም ከ100 በላይ የመንግስታቱ አባል ሀገራት የመዋቅር ለውጥ የሚል ሰነድ ላይ ፈርመዋል፡፡በነገራችን ላይ በ ዚሁ የተባበሩት መንግስታት የ አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እስከ ዚህ ወር መጨረሻ የሚደረግ ሲሆን በተለይ ከ ሴፕቴምበር 19 የሚጀምረው የ መሪዎች አጀንዳ ውይይት ሃገሮች በተለየዩ ርዕሰ ጉዳዮች ያላቸውን አቋም ያስተጋባሉ፤አሜሪካ ቻይና ጃፓን በሰሜን ኮር ያ ላይ ሊወስዱ የሚችሉትን አቋሞች ያንፀባርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ በ ዚሁ 72ኛ የተባባሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማፘም ደሳለኝ የተመራ የልዑካን ቡድን መገኘቱ ታውቀዋል::