Thursday, September 28, 2017

የሳዑዲ ሴቶች መኪና ነዱ

ሳዑዲ አረቢያ ከሴቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥሯን ማንሳቷን ቀጥላለች ፡፡ አሁን ደግሞ ለአመታት ከልክላው የነበረውን የሴቶች መኪና ማሽከርከርን ፈቅጃለሁ ብላለች፡፡
ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴት ሳዑዲ አረቢያዊያን መንጃ ፈቃድ እየተቀበሉ ማሽከርከር የሚችሉበትን መንገድ አውጥቼ እያወረድኩ ነው ብላ ደስ አሰኝታቸዋለች፡፡
የሳዑዲ ሴቶች መታወቂያ እንጂ መንጃ ፍቃድ ስለሌላቸው ሁሌም ጋቢና የሚቀመጡት በተጓዥ ወንበር ላይ ብቻ ነበር፡፡
አሁን ግን ያ ታሪክ ሆኖ ይቀራል ሴቶች የመረጡትን መኪና በፈለጉት አውራ ጎዳና ላይ ከወንዶች ጋር እየተያዩ ይጋልባሉ የሚል ዜናን ጽፎ ያስነበበው የሀገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡

ነገር ግን አሁንም ድረስ ሴት ሳዑዲ አረቢያዊያን ብቻቸውን መጓዝ ፤ፓስፖርት ማውጣት ፣ የፈለጉትን ማግባት፤ የባንክ ሂሳብ መክፈት እና ንግድ መጀመር አጥብቀው ይከለከላሉ፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...