የአሜሪካ ደሴት ናት የተባለችውን ፖርቶሮኮ
ሄሪከን ኢርማና ሄሪከን ማሪያ ተፈራርቀው ካፈራረሷት ወዲህ የሚበላ ምግብና የሚጠጣ ንፁህ ውሃ ከሀገሪቱ እየጠፋ ነው ተባለ፡፡
ጨለማን መከላከል የሚያስችለው የአሌክትሪክ
መብራት እንኳን ከጠፋና ማከፋፈያዎቹ ከፈራረሱ 2 ሳምንት አልፈዋል፡፡
በዚህ ሳቢያም 3.4 ሚሊዮን ነዋሪዎች
ሌት በዳሰሳ እንደሚንቀሳቀሱ አስተዳዳሪዎቹ በዚህችው ፖርቶሪኮ የሚኖሩ ነዋሪዎች የአሜሪካ ዜጎች በመሆናቸው ተገቢውን እርዳታ አላገኘንም
በእኩል አይን እንታይ ብለው አቤቱታ አቅርበው በጎ ምላሽ አግኝተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ
ተነስተው ወደ ደሴቷ የሚጓዙ መርከቦችን አስናድተው ምግብ፤ መጠጥና የህክምና እቃዎች እንዲሄዱላቸው አዘዋል፡፡
መርከቧ የባህር ሃይል ስትሆን በውስጧ
መታከሚያና የመኝታ ክፍሎች እንዳሏት ተጠቁሟል፡፡ ፖርቶ ሪካአዊያን በወጀቡ ምክንያት የጤና እክል ገጥሟቸው ከሆነ ነፃ ህክምና ያሰጣቸዋል
ተብሏል፡፡