Thursday, September 28, 2017

የአሜሪካ ስደተኞች ወጭ…

በህገወጥ መንገድ ወደ ሰሜን አሜሪካ ገብተው የከተሙ የሌላ ሀገር ዜጎች መንግስትን 135 ቢሊዮን ዶላር አመታዊ ወጪ እያስወጡት ነው ተባለ፡፡
እነዚህ 12 ሚሊዮን ይበልጣሉ የተባሉት ስደተኞችና የነሱ ልጆች የሆኑ 4 ሚሊዮን ታዳጊዎች የአሜሪካን ህዝብ ሳይፈልግ ተጨማሪ ግብር እንዲከፍል አስገድደውታል፡፡
በተለይ እነዚህ ስደተኞች በብዛት ይኖሩባታል ተብላ የምትገመተው ኒዮርክ ለእያንዳንዱ ህገወጥ ስደተኛ 25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወጪ በየአመቱ እንደምታወጣ ታውቋል፡፡
ይህ ገንዘብ በቀጥታ ለተሰዳጆቹ እየተሰጠ ባይሆንም እነሱን አድኖ ለመያዝ የሚመደቡት ፖሊሶች ቁጥር ሁሉ እንዲጨምር ተደርጓል፡፡ ድንገት ታመው ሆስፒታል ሲገቡ የሚታከሙበት ገንዘብ ስለማይኖራቸው መንግስት ይሸፍንላቸዋል ለልጆቻቸውም የትምህርት ወጪ ይከፍልላቸዋል፡፡
ታዲያ ህገወጥ ናቸው ተብለው ከሀገሪቱ ለመባረር በስም ዝርዝር የተያዙት ሰዎች ለመንግስት የከፈሉት ግብር እና በምላሹ የወጣላቸው ወጪ በየትኛውም መንገድ አልተገናኘም ሲሉ የትራምፕ አስተዳደር የሂሳብ ሰራተኞች አስልተዋል፡፡

በቀጣይም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቃል ገብተው እስካሁን ሳያስፈጽሙት ከቆዩት መካከል የታክስ ስርአቱን ማሻሻል ነበር፡፡ በዚህ የታክስ ስርአታቸው እጅግ ሀብታምና ከፍተኛ ገቢ አላቸው ከሚባሉ አሜሪካውያን ይገኝ የነበረው የታክስ ገንዘብ እስከ 35 በመቶ በመቀነስ ለነሱ እፎይታን ሲያጎናጽፍ የታችኛው ክፍል ዜጎችን ለማስጨነቅ ተነስተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ግዛቶች ከባለ ሀብቶች የሚያገኙት ገቢ ይቀንስባቸዋል እና ለህገወጥ ስደተኞች ያደረጉት የነበረ ውን የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ስለሚቀንሱ በተዘዋዋሪ ስደተኞቹ አማራጭ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...