Wednesday, September 27, 2017

መሬት ክብ ናት?!


መሬት ክብ ናት የሚለውን የጂዮግራፊ ፅንስ ሃሳብ ብማረውም፤ መፃህፍትን አገላብጩ ባነብም ሊዋጥልኝ አልቻለም በማለት ከራሱ ጋር ሙግተ የገጠመው አሜሪካዊ ራፐር ቢኦቢ እራሴው ሳተላይት አምጥቄ እደርስበታለሁ በማለት የገንዘብ እርዳታ እያሰባሰበ ይገኛል፡፡

ራፐሩ እንደዚህ የልብ ልብ የተሰማውና የናሳን የምርምር ውጤት ያጣጣለው ከብዙ ጊዜያት በፊት ቢሆንም አሁን ግን ታሪክ መስራት እፈልጋለሁ ብሎ ቢያንስ እውነታውን ማወቅ የፈለገ ሰው ብር ያዋጣ ብሎ 200 ሺህ የአሜርካን ዶለር ግብ አስቀምጧል፡፡
ራፐሩ በተለያዩ የቴልቪዥንና የሬድዮ ፕግራሞች ላይ ቀርቦ በተናገረው ቃሉ እንዲህ ብሏል፡፡ መሬት ክብ ሆና ቢሆን ከአቀበት ወደ ቁልቁል ስታዘም እኛ እንወድቀ አሊያም እንገዳገድ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ባለመሆኑ ከምዕት አመታት በፊት ይከራከሩ ከነበሩ የመሬት ተመራማሪዎች ጋር ሃሳቤን ደምሬው ሳይንስን እቃወማለሁ ብሏል፡፡


 በትሪሊዮን ዶለሮች ወጪ ምርምር የሚያካሂደው ናሳ የራፐሩን የማወቅ ጉጉት ቢያደንቅም መቶ ሺህ መፅሃፍትን አንብቦ እና ሳይንስን በጥልቀት ተረድቶ እንኳን አንበቦ የማይደርስበትን ሃሳብ ማንሳቱ ደፋር ነው ብሎታል እስካሁንም ያሰባሰው ገንዘብ 650 ዩኤስዲ ነው፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...