Wednesday, September 27, 2017

የአሜሪካ የዓመቱ ብሔራዊ አስተማሪ ኢትዮጵያን ጎበኝች

የአሜሪካ የዓመቱ ብሔራዊ  አስተማሪ ኢትዮጵያን ጎበኝች፡፡አሸናፊም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተገኝታ ከአስተማሪዎች እና ተማሪዎች ጋር ተወያይታለች፡፡


National teacher of the year ወይም የዓመቱ ብሄራዊ መምህር በአሜሪካን ሀገር የሚሰጥ ሙያዊ ሽልማት ነው፡፡ ይህ ሽልማት በ1952 ዓ.ም ነው የማስተማርን ከፍተኛ ችሎታ እውቅና የመስጠት አላማ ይዞ የተጀመረው፡፡
ከሁሉም የአሜሪካን ግዛቶች ከተወከሉ መምህራን መካከል የዚህ ማዕረግ አሸናፊ የሆነው መምህር በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ለሙያው እንደ ቃል አቀባይ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የዘንድሮው የብሔራዊ አስተማሪ ማዕረግ አሸናፊ ሲድኒ ቻፍ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጋለች፡፡
ለአንድ ዓመት በሚቆየው የመምህርነት ሙያ ቃል አቀባይነት ግልጋሎቷ ከአሜሪካ ወጪ የመጀመሪያዋ የሆነው ጉብኝት ነው በኢትዮጵያ ያደረገችው::
በቆይታዋ አንድነት ፣ ስኩልኦፍ ቱሞሮ እና ቦሌ መድሀኒአለም ትምህርት ቤቶች በመገኘት ከመምህራን እና ከተማሪዎች ጋር ተወያይታለች፡፡

በዚህም በተለይም የታሪክ ትምህርትን በመጠቀም አለምን መቀየር የሚቻልበትን መንገድ መምህራን ለተማሪዎቻቸው እንዴት ማመላከት እንደሚገባቸው ገለፃ አድርጋለች ተብሏል፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...