ምዝገባው ከኦክቶበር 3 እስከ ኖቬምበር 7 የሚቀይ ሲሆን በዚህ
ፕሮግራም ከሁሉም የአለማችን ክፍሎች በአጠቃላይ 50000 አመልካቾች እንደሚቀበሉም ተገልጿል፡፡
የዲቪ አመልካቾች የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው
ያጠናቀቁ እና የከፍተኛ ተቋም መግብያ ውጤት ያላቸው አልያም የዲግሪ ምሩቅ መሆን አለባቸው፡፡ የቴክኒክ እና ሞያ ስልጠና ግን እንደትምህርት
ማስረጃ እንደማያገለግል ኤምባሲው በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡
አመልካቾች በድርጅቱ ድህረገፅ dvlottery.state.gov በመጠቀም ብቻ መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን onetonline.org በመግባት ደግሞ
ለማመልከት ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ተብሏል፡፡ አመልካቾች አንዴ ብቻ ማመልከት የሚችሉ ሲሆን በተደጋጋሚ ቅፁን መሙላት
ግን ከምዝገባው ውጪ እንደሚያደርጋቸው ተገልጿል፡፡ ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ የማይጠይቅ ሲሆን ኢምባሲው ክፍያ የሚጠየቀው
ለቃለ-መጠይቅ ያለፉ እድለኞችን ብቻ ነው ተብሏል፡፡
ለደህንነት ሲባል ኤምባሲው ለዲቪ እድለኞች ኢሜል የማይልክ ሲሆን
ከ ሜይ 1 2018 ጀምሮ አመልካቾች የተሰጣቸው የሚስጥር ቁጥር በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡