Tuesday, September 19, 2017

የአውሮፓ ህብረት መስሪያ ቤት ለአባል ሀገሪቱ ነዋሪዎች ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት የ143 ሚሊዮን ዶላር በጀት መበጀቱ ተሰማ፡፡

ዝቅተኛና ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አውሮፓውያን አንድ ለማድረግ አስቧል የተባለው ይህ ፕሮግራም በመጪው አመት መጀመሪያ አካባቢ ይከፈታል ተብሏል፡፡ በአባል ሀገራቱ ህዝባዊ መዝናኛ ቦታዎች በቤተመፅሃፍትና በጤና ተቋማት ፈጣን የኢንተርኔት አስተላላፊ መሳሪያዎች ተገጥመው ዜጎች ያለምንም ገመድ ንክኪ በዋይፋይ ብቻ ጎግል ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ምግባና መጠጥ ለሁሉም ዜጎች በእኩል መጠን ማቅረብ ባልችልም መረጃዎችን መመገብ ግን አያቅተኝም ብሎ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ይህነ የበጎ አድርጎት የገመድ አልባ ኢንተርኔት ፕሮግራም በ6000 ቦታዎች ላይ ለመጀመር ዕቅድ ወጥቶ ባለሙያዎች ለስራው እየተፈለጉ እደሆነም ተነግሯል፡፡ የትኛውም ለህዝብ እስራለሁ የሚል ተቋም ቅድሚያ መጠየቂያ ደብዳቤ ካስገባ ያለ ምንም ክፍያ በህንፃው አሊያም በጊቢው ውስጥ ተተክሎለት አላፊው አግዳሚው እንዲጠቀምበት ያደርጋል ብሎ የአውሮፓ ህብረት ቅስቀሳ በማደረግ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ የልግስና ፕሮግራም ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ ጨዋታ መኖሩን ተመልክተናል የሚሉ የህብረቱ ፓለቲከኞች ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅርበው ውሳኝ መረጃ ሊሰበስቡበት የታለመ አደገኛ ተግባር ነው በማለት የሚኮንኑትም አልጠፉም

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...