Tuesday, October 3, 2017

አፍሪካ ፋሽን ሪስፕሽን አዲስ አበባ ኤንድ ፓሪስ በሚል ርዕስ የፋሽን ትርኢት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሄደ፡፡

አፍሪካ ፋሽን ሪስፕሽን  መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገ የፋሽን ድርጅት ሲሆን ትርኢቱ ሲያቀርብ ይህ አራተኛ ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ትርኢቶች  በፓሪስ የተዘጋጀ ሲሆን የአፍሪካ ፋሽን ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ የህብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ቢዘጋጅ የተሻለ ነው በማለት ሶስተኛው እና አራተኛ ዙር ትርኢቶች በአዲስ አበባ እንዲዘጋጅ መደረጉ ሰምተናል፡፡
በዚህ ዝግጅት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ከ15 የሚበልጡ ዲዛይነሮች እና ሞዴሎች የተሳተፉ ሲሆን ዲዛይነሮቹ የሀገራቸውን ባህል ያሳያሉ ያሏቸውን ዘመናዊ ልብሶቻቸው አቅርበዋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ በመወከል ወ/ሮ እጅጋየሁ ሃይለ ጊዮርጊስ ከእጅ ጥበብ ስራዎቿን አቅርባ ነበር፡፡

የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...