Thursday, September 28, 2017

Ketezegaw Dose Season 1 - EP 44

Yebeteseb Chewata Season 2 - EP 26

የሳዑዲ ሴቶች መኪና ነዱ

ሳዑዲ አረቢያ ከሴቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥሯን ማንሳቷን ቀጥላለች ፡፡ አሁን ደግሞ ለአመታት ከልክላው የነበረውን የሴቶች መኪና ማሽከርከርን ፈቅጃለሁ ብላለች፡፡
ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴት ሳዑዲ አረቢያዊያን መንጃ ፈቃድ እየተቀበሉ ማሽከርከር የሚችሉበትን መንገድ አውጥቼ እያወረድኩ ነው ብላ ደስ አሰኝታቸዋለች፡፡
የሳዑዲ ሴቶች መታወቂያ እንጂ መንጃ ፍቃድ ስለሌላቸው ሁሌም ጋቢና የሚቀመጡት በተጓዥ ወንበር ላይ ብቻ ነበር፡፡
አሁን ግን ያ ታሪክ ሆኖ ይቀራል ሴቶች የመረጡትን መኪና በፈለጉት አውራ ጎዳና ላይ ከወንዶች ጋር እየተያዩ ይጋልባሉ የሚል ዜናን ጽፎ ያስነበበው የሀገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡

ነገር ግን አሁንም ድረስ ሴት ሳዑዲ አረቢያዊያን ብቻቸውን መጓዝ ፤ፓስፖርት ማውጣት ፣ የፈለጉትን ማግባት፤ የባንክ ሂሳብ መክፈት እና ንግድ መጀመር አጥብቀው ይከለከላሉ፡፡

እርዳታ ለፖርቶሪኮ

የአሜሪካ ደሴት ናት የተባለችውን ፖርቶሮኮ ሄሪከን ኢርማና ሄሪከን ማሪያ ተፈራርቀው ካፈራረሷት ወዲህ የሚበላ ምግብና የሚጠጣ ንፁህ ውሃ ከሀገሪቱ እየጠፋ ነው ተባለ፡፡
ጨለማን መከላከል የሚያስችለው የአሌክትሪክ መብራት እንኳን ከጠፋና ማከፋፈያዎቹ ከፈራረሱ 2 ሳምንት አልፈዋል፡፡
በዚህ ሳቢያም 3.4 ሚሊዮን ነዋሪዎች ሌት በዳሰሳ እንደሚንቀሳቀሱ አስተዳዳሪዎቹ በዚህችው ፖርቶሪኮ የሚኖሩ ነዋሪዎች የአሜሪካ ዜጎች በመሆናቸው ተገቢውን እርዳታ አላገኘንም በእኩል አይን እንታይ ብለው አቤቱታ አቅርበው በጎ ምላሽ አግኝተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ተነስተው ወደ ደሴቷ የሚጓዙ መርከቦችን አስናድተው ምግብ፤ መጠጥና የህክምና እቃዎች እንዲሄዱላቸው አዘዋል፡፡

መርከቧ የባህር ሃይል ስትሆን በውስጧ መታከሚያና የመኝታ ክፍሎች እንዳሏት ተጠቁሟል፡፡ ፖርቶ ሪካአዊያን በወጀቡ ምክንያት የጤና እክል ገጥሟቸው ከሆነ ነፃ ህክምና ያሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ስደተኞች ወጭ…

በህገወጥ መንገድ ወደ ሰሜን አሜሪካ ገብተው የከተሙ የሌላ ሀገር ዜጎች መንግስትን 135 ቢሊዮን ዶላር አመታዊ ወጪ እያስወጡት ነው ተባለ፡፡
እነዚህ 12 ሚሊዮን ይበልጣሉ የተባሉት ስደተኞችና የነሱ ልጆች የሆኑ 4 ሚሊዮን ታዳጊዎች የአሜሪካን ህዝብ ሳይፈልግ ተጨማሪ ግብር እንዲከፍል አስገድደውታል፡፡
በተለይ እነዚህ ስደተኞች በብዛት ይኖሩባታል ተብላ የምትገመተው ኒዮርክ ለእያንዳንዱ ህገወጥ ስደተኛ 25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወጪ በየአመቱ እንደምታወጣ ታውቋል፡፡
ይህ ገንዘብ በቀጥታ ለተሰዳጆቹ እየተሰጠ ባይሆንም እነሱን አድኖ ለመያዝ የሚመደቡት ፖሊሶች ቁጥር ሁሉ እንዲጨምር ተደርጓል፡፡ ድንገት ታመው ሆስፒታል ሲገቡ የሚታከሙበት ገንዘብ ስለማይኖራቸው መንግስት ይሸፍንላቸዋል ለልጆቻቸውም የትምህርት ወጪ ይከፍልላቸዋል፡፡
ታዲያ ህገወጥ ናቸው ተብለው ከሀገሪቱ ለመባረር በስም ዝርዝር የተያዙት ሰዎች ለመንግስት የከፈሉት ግብር እና በምላሹ የወጣላቸው ወጪ በየትኛውም መንገድ አልተገናኘም ሲሉ የትራምፕ አስተዳደር የሂሳብ ሰራተኞች አስልተዋል፡፡

በቀጣይም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቃል ገብተው እስካሁን ሳያስፈጽሙት ከቆዩት መካከል የታክስ ስርአቱን ማሻሻል ነበር፡፡ በዚህ የታክስ ስርአታቸው እጅግ ሀብታምና ከፍተኛ ገቢ አላቸው ከሚባሉ አሜሪካውያን ይገኝ የነበረው የታክስ ገንዘብ እስከ 35 በመቶ በመቀነስ ለነሱ እፎይታን ሲያጎናጽፍ የታችኛው ክፍል ዜጎችን ለማስጨነቅ ተነስተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ግዛቶች ከባለ ሀብቶች የሚያገኙት ገቢ ይቀንስባቸዋል እና ለህገወጥ ስደተኞች ያደረጉት የነበረ ውን የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ስለሚቀንሱ በተዘዋዋሪ ስደተኞቹ አማራጭ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

Wednesday, September 27, 2017

EBS Special Mesekel Show - Part 2/ With the Winner Families of Yebeteseb...

EBS Special Mesekel Show with Friyat & Alemayehu - Part 1

Yebeteseb Chewata Season 2 - EP 25

Yebeteseb Chewata: Special Meskel Show/ Final/ የሲዝኑ ፍፃሜ የ መኪና ሽልማት ስነስርአት

Yebeteseb Chewata: Meskel Special Semi Final Show

የአሜሪካ የዓመቱ ብሔራዊ አስተማሪ ኢትዮጵያን ጎበኝች

የአሜሪካ የዓመቱ ብሔራዊ  አስተማሪ ኢትዮጵያን ጎበኝች፡፡አሸናፊም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተገኝታ ከአስተማሪዎች እና ተማሪዎች ጋር ተወያይታለች፡፡


National teacher of the year ወይም የዓመቱ ብሄራዊ መምህር በአሜሪካን ሀገር የሚሰጥ ሙያዊ ሽልማት ነው፡፡ ይህ ሽልማት በ1952 ዓ.ም ነው የማስተማርን ከፍተኛ ችሎታ እውቅና የመስጠት አላማ ይዞ የተጀመረው፡፡
ከሁሉም የአሜሪካን ግዛቶች ከተወከሉ መምህራን መካከል የዚህ ማዕረግ አሸናፊ የሆነው መምህር በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ለሙያው እንደ ቃል አቀባይ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የዘንድሮው የብሔራዊ አስተማሪ ማዕረግ አሸናፊ ሲድኒ ቻፍ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጋለች፡፡
ለአንድ ዓመት በሚቆየው የመምህርነት ሙያ ቃል አቀባይነት ግልጋሎቷ ከአሜሪካ ወጪ የመጀመሪያዋ የሆነው ጉብኝት ነው በኢትዮጵያ ያደረገችው::
በቆይታዋ አንድነት ፣ ስኩልኦፍ ቱሞሮ እና ቦሌ መድሀኒአለም ትምህርት ቤቶች በመገኘት ከመምህራን እና ከተማሪዎች ጋር ተወያይታለች፡፡

በዚህም በተለይም የታሪክ ትምህርትን በመጠቀም አለምን መቀየር የሚቻልበትን መንገድ መምህራን ለተማሪዎቻቸው እንዴት ማመላከት እንደሚገባቸው ገለፃ አድርጋለች ተብሏል፡፡

መሬት ክብ ናት?!


መሬት ክብ ናት የሚለውን የጂዮግራፊ ፅንስ ሃሳብ ብማረውም፤ መፃህፍትን አገላብጩ ባነብም ሊዋጥልኝ አልቻለም በማለት ከራሱ ጋር ሙግተ የገጠመው አሜሪካዊ ራፐር ቢኦቢ እራሴው ሳተላይት አምጥቄ እደርስበታለሁ በማለት የገንዘብ እርዳታ እያሰባሰበ ይገኛል፡፡

ራፐሩ እንደዚህ የልብ ልብ የተሰማውና የናሳን የምርምር ውጤት ያጣጣለው ከብዙ ጊዜያት በፊት ቢሆንም አሁን ግን ታሪክ መስራት እፈልጋለሁ ብሎ ቢያንስ እውነታውን ማወቅ የፈለገ ሰው ብር ያዋጣ ብሎ 200 ሺህ የአሜርካን ዶለር ግብ አስቀምጧል፡፡
ራፐሩ በተለያዩ የቴልቪዥንና የሬድዮ ፕግራሞች ላይ ቀርቦ በተናገረው ቃሉ እንዲህ ብሏል፡፡ መሬት ክብ ሆና ቢሆን ከአቀበት ወደ ቁልቁል ስታዘም እኛ እንወድቀ አሊያም እንገዳገድ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ባለመሆኑ ከምዕት አመታት በፊት ይከራከሩ ከነበሩ የመሬት ተመራማሪዎች ጋር ሃሳቤን ደምሬው ሳይንስን እቃወማለሁ ብሏል፡፡


 በትሪሊዮን ዶለሮች ወጪ ምርምር የሚያካሂደው ናሳ የራፐሩን የማወቅ ጉጉት ቢያደንቅም መቶ ሺህ መፅሃፍትን አንብቦ እና ሳይንስን በጥልቀት ተረድቶ እንኳን አንበቦ የማይደርስበትን ሃሳብ ማንሳቱ ደፋር ነው ብሎታል እስካሁንም ያሰባሰው ገንዘብ 650 ዩኤስዲ ነው፡፡

What's New: አወዛጋቢው መንገድ

Monday, September 25, 2017

የአዲስ ነገር የአለም አበይት ክስተቶች!


  • በመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ማስፈራሪያ ዛቻ የደረሳት ኢራን አልበገርም በማለት 2000 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘግ ሚሳኤል አስወነጨፈች ፣ድርጊቱ ያች ሀገር ከእስራኤል ጋር ያላትን ፍጥጫ እንዳያጦዘው ተሰግቷል፡፡

  •  ለአራተኛ የስልጣን ዘመን በምርጫ የተሳተፉት የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጄላ ሜርኬል ድል ቀንቷቸዋል ፡፡ ለድላቸውም መራጮች በስደተኞች ጉዳይ ያላቸውን አቋም መቀየራቸው እንደምክንያት እየተጠቀሰ ነው፡፡

  •  የሳዑዲ አረብያ መንግሥት ለሴቶች የተሻለ መብት መስጠት በአገሪቱ ብሔራዊ በዓል ላይ ከወንዶች እኩል አደባባይ ወጥተው እንዲያከብሩ ፈቀደች፡፡ እርምጃው የሳዑዲ አረቢያን ጉሳዊ መንግሥት ያዝኩት ያለው እርምጃ አካል ቢሆንም የሳዑዲ ሴቶች ተጨማሪ መብቶቻቸውን እየጠየቁ ነው፡፡

  •  የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስአይድ) በአፍሪካ ሀገራት ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የወባ በሽታ ለመግታትና ብሎም ለማጥፋት ተጨማሪ ሀገራትን በፕሮግራሜ ውስጥ አስገብቻለሁ ሲል በሃላፊው ማርክ ግሪን በኩል አሳውቋል፡፡በበጀት መልክ መድቦ ሊንቀሳቀስባቸው ያሰባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ካሜሮንን፣ ኮትዲቫርን ፣ኒጀርን እና ሴራሊዮንን መሆኑ ተነግሯል

  •  ታላቋ ብሪታንያ የአሲድ ጥቃት ላደረሰ ግለሰብ ከፍተኛ የእስር ቅጣት እንደምትጥል ካሳወቀች 2ወር እንኳ ባይሞላትም ድርጊቱ ሊቆም እንዳልቻለ የአገሪቱ ፖሊስ አሳውቋል፡፡ በአንድ የገበያ አዳራሹ መውጫና መግቢያ ላይ በትርምስምስ መሃል ዝርፊያን ሊፈጽሙ የፈለጉ ወጣቶች በሰዎች ፊት ላይ አቃጣይ ፈሳሽ ረጭተው ስድስት ሰዎችን እንደጎዱ ታውቋል፡፡ ፖሊስ ክትትል አድርጎ አንድ ወንጀለኛ ብቻ ቢይዝም ቀሪዎቹ አምስቱ ገና እንዳልተያዙ አሳውቋል፡፡


Ketezegaw Dose Season 2 - EP 43

Yetekeberew (የተቀበረው) EBS Series Drama Season 1 - EP 1

Friday, September 22, 2017

አዲሱ ብርቱ ቅጣት ለሰሜን ኮሪያን !


ካሳሁን መብራቱ - ለአዲስነገር ከዋሽንግተን ዲሲ


እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ በሀገሪቱ ላይ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ረገጣ  ለማስቆምና የባሊስቲክ ሚሳኤል ግንባታን እንድትገታ በሚል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 9 ያህል ማዕቀብ የተጣለባት ሰሜን ኮሪያ መስማት እንጂ መተግበር ላይ ደካማ ናት ተብሏል፡፡
በቅርቡ እንኳን  አሜሪካ በግሏ እና ከተባበሩት መንግስታት ጋር አብራ የሰሜን ኮሪያን ኢኮኖሚ የሚሸነቁጥ ማዕቀብ ቢያወርዱባትም ለሌላኛው የሚሳኤል ሙከራ እየተዘጋጀች መሆኗን ፍንጭ ሰጥታለች፡፡

የነዳጅ እና የጨርቃ ጨርቅ ምርቶቿ ከሀገሯ ወጥተው በዓለም ገበያ እንዳይሸጡ ሲታገዱባት መውጫ ቀዳዳ አለኝ ብላ ያሳወቀችው አለማቀፍ የውጭ ባንኮችን በሰለጠኑ ባለሙያዎቿ ማዘረፍና ለፕሮግራሟ ድጎማ ማድረግ ነበር፡፡
ታዲያ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከአሁን አሁን ለሃሳቤ ተገዛች ለቁጣዬ ደነገጠች እያሉ ቢጠባበቁም ያሰቡት ሳይሳካ እዚህ ደርሰዋል፡፡ በንዴት ቃለ አጠፋታለሁ እያሉ ሲዝቱም ተሰምቷል፡፡
አሁን ግን ከአማካሪዎቼ ጋር ተወያይቼ ያመጣሁት የቅጣት ሃሳብ ብርቱ ነው በማለት አዲስ ሰሜን ኮሪያን የሚመለከት ሰነድ ፈርመው ስራ ላይ እንዲውል አዘዋል፡፡
ፊርማቸው ያረፈበት አዲስ ተፈጻሚ ህግ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የሚሰሩ ሀገራት ብቻ ሳይሆን ተቋማት ግንኙነታቸውን ማቆም እንዳለባቸው የሚደነግግ ነው፡፡
በየትኛውም ሀገር የሚገኙ የቢዝነስ ተቋማት በቀጥታም ይሁን በስውር ከሰሜን ኮሪያ ጋር የሚያነካካ ስራ ካላቸው ይህንኑ ማቆም እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡
እነሱም ጥቅማችን ይቀራል ብለው ካሰቡ ከአሜሪካ ጋር የሚኖራቸውም ቁርኝት ይቋረጥባቸዋል ብለዋል ትራምፕ፡፡ በስተመጨረሻም ቢሆን ትራምፕና አስተዳደራቸው ያፈለቁት አዲሱ የመቅጫ ሰነድ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
በተለይ የቻይና እናየሌሎች የኢሲያ ሀገራት ብሄራዊ ባንኮች ከሰሜን ኮሪያ እየፈረሰች እና እየደኸየች  ያለች ሀገር በመሆኗ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር መነገድ ኪሳራና ከአሜሪካ ጋር  መቃቃር ደግሞ ስራን በገዛ እጅ ማጣት ነው ያሉ ድርጅቶች ወዲያው ይሁንታቸውን ለትራምፕ አሳይተዋል በማለት ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡

የማሪያ ወጀብ ! በደቡባዊ እና ማእከላዊ አሜሪካ


ካሳሁን መብራቱ - ለአዲስነገር ከዋሽንግተን ዲሲ
በእንስት ስም የምትጠራው የማሪያ ወጀብ የፓርቶሪኮንና የዶሚኒካን ሀገራትን ቶሎ እንዳያገግሙ አድርጋ አፈራርሳቸዋለች ተብላለች፡፡ ዝናብን ከፈጣን አውሎ ንፋስ ጋር ቀላቅላ ምድሪቱን ያጥለቀለቀችው የማሪያ ወጀብ ትላልቅ ህንፃዎች በመጉዳት አስፋልቶች አፈራርሳለች በተለይ Porto rico በተባለች የዴሴት ሀገር ላይ የከፋ ጉዳት አድርሳ ህይወት ነጥቃለች፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ተቋቁሞ ለህዝቦቹ የኤሌክትሪከ አገልግሎት የሚሰጠው ብቸኛው የመብራት ማከፋፈያ ማእከሏ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለማደስና ዳግም ብርሃን ለመርጨት ቢያንስ 4-6 ወራት ይፈጃል ተብሏል፡፡


የ አዲስ ነገር  ልዩ ጥንቅር... በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አከራካሪው የአሜሪካ የታክስ ማሻሻያ ሁለቱን አውራ ፓርቲዎች ለሁለት ከፍሎ ሲያነታርክ ቆ...